አካዳሚው በ8ኛው ሀገር አቀፋ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ምዘና ውድድር ላይ ለ2018 በጀት አመት እጩ ሰልጣኞችን እየመለመለ ነው
ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋር ባዘጋጀው ከጥር 27/2017 ዓ.ም እስከ የካቲት 05/2017 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ "የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለአሸናፊ ሀገር" በሚል መሪ ሀሳብ በሚቆየው 8ኛው ሀገር አቀፋ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ምዘና ውድድር ላይ አካዳሚው ለ2018 በጀት አመት በተለያዩ ስፖርቶች እጩ ሰልጣኞችን እየመለመለ ነው።
አካዳሚው በምልመላው ከአካዳሚው አዲስ አበባ ካምፓስ እና አሰላ ካምፓስ (ከአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል) የተውጣጡ አሰልጣኞች፣የስፖርት ሙያተኞች፣የህክምና ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። አካዳሚው ከዚህ ቀደም ከመሰል የታዳጊ ምዘና ውድድሮች ላይ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተተኪ ታዳጊዎችን መልምሎ በማሰልጠን በአህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ሀገራቸውን ማስጠራት የቻሉ በርካታ ተተኪዎችን ማፍራቱ ይታወቃል።