የወርልድ ቴኳንዶ ዲፓርትመንት የቴኳንዶን አካላዊ ቅልጥፍና ከአዕምሯዊ ጥንካሬ ጋር በማቀናጀት ሁለገብ አትሌቶችን ለመፍጠር ይሠራል። የስፓሪንግ ቴክኒኮችን፣ ራስን የመከላከል ስትራቴጂዎችን እና ፓተርኖችን ማዳበር ላይ በማተኮር አትሌቶች አካላዊ እና አዕምሯዊ ጥንካሬያቸውን የሚያጎለብቱበት ጥብቅ ስልጠና ያገኛሉ። ዲፓርትመንቱ እንደ ክብር፣ ትኩረት ኣና ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብ ያሉ እሴቶችን በማስረጽ የመልካም ባህሪ ግንባታ ላይ ጠንካራ አጽንዖት ይሰጣል። አትሌቶች በሚያገኙት የጥንካሬ እና የመለጠጥ ስልጠናዎች ተደግፈው በማርሻል አርትስ ውድድሮች ላይ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ አካላዊ ገጽታዎችን ያዳብራሉ። የወርልድ ቴኳንዶ ዲፓርትመንት አትሌቶች ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ በወርልድ ቴኳንዶ ፌደሬሽን ፈቃድ ባገኙ ውድድሮች ለመወዳደር ብቁ የሚያደርግ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ቀላል የማይባሉ ተወዳዳሪዎችን ያፈራል።