የዋና ዲፓርትመንት ልዩ ቴክኒካዊ ብቃት፣ ብርታት እና የውድድር መንፈስ የተላበሱ አትሌቶችን ለማፍራት የተቋቋመ ነው። ውሃ መቅዘፍ፣ አዟዟር እና አጀማመርን በማዳበር ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውኃ ውስጥ የላቀ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ ይረዳል። የጥንካሬ እና የአካል ብቃት ፕሮግራሞች የዋና ውድድር ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልገውን ብርታት የሚገነቡ ሲሆን፣ የኦሎምፒክ ስታንዳርድ መዋኛ ገንዳዎች እና የስልጠና መሣሪያዎች ተደራሽነት ደግሞ አትሌቶች ዘመናዊ በሆነ ሁኔታ መሰልጠናቸውን ያረጋግጣሉ። ዋናተኞችን ከሀገር ውስጥ ውድድሮች ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ መድረኮች ድረስ ባሉ የተለያዩ ደረጃዎች እንዲወዳደሩ የሚያዘጋጀው የዋና ዲፓርትመንት በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን አሸናፊም በመሆን ለኢትዮጵያ ኩራት የሚሆኑ አትሌቶችን ለማፍራት ያልማል።