የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የምርምር ዓላማዎች እና አገልግሎቶች

የምርምር ዓላማዎች እና አገልግሎቶች

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ፦ ለልህቀት እና ፈጠራ በስፖርት ሳይንስ ምርምር ግንባር ቀደም መሪ

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በስፖርት ሳይንስ የልህቀት እና የፈጠራ ተምሳሌት ሲሆን፣ በዘመን አመጣሽ ምርምር እና ተጽዕኖ አሳዳሪ ተነሳሽነቶች አማካኝነት የአትሌቲክስን የወደፊት ገጽታ ለመቅረጽ ይሠራል። በየጊዜው የሚለዋወጡትን የአትሌቶች፣ የአሠልጣኞች እና የሰፊው የስፖርት ማኅበረሰብ ፍላጎቶች ለማሟላት ቁርጠኛ የሆነው አካዳሚ በኢትዮጵያ እና ከዚያም ባሻገር የስፖርት እድገትን ከፊት ሆኖ እየመራ ይገኛል።

መረጃ ላይ በተመሠረተ ምርምር የስፖርት ዘርፍን ማሳደግ

የአካዳሚው የምርምር ዓላማዎች የስልጠና ዘዴዎችን ውጤታማነት ለማሳደግ፣ የስፖርት አስተዳደር አሠራሮችን ለማሻሻል እና እንደ የተሰጥዖ ልየታ፣ ስፖርታዊ አመጋገብ እና ጉዳት የመከላከል ሥራ የመሣሰሉ ቁልፍ መስኮች ውስጥ አዳዲስ ፈጠራዎችን ለማግኘት በጥንቃቄ የተበጁ ናቸው። የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጥያቄን በመጠየቅ እና መረጃ ላይ የተመሠረተ አሠራርን በመተግበር የሚለይ ባህል በማዳበር ፕሮግራሞች ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ብቻ ሳይሆን ከዚያም የተሻሉ መሆን መቻላቸውን ያረጋግጣል።

ለስፖርታዊ ምርምር የሚያገለግል የትብብር ማዕከል

አካዳሚው ለስፖርታዊ ምርምር እና የምክር አገልግሎት የተዋጣለት ማዕከል እንደመሆኑ መጠን በስፖርት ዓለም ያሉ አሳሳቢ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ አካላትን የሚያሰባስብ የዩንቨርስቲዎች፣ የግል ተመራማሪዎች እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መረብን ይፈጥራል። ዋነኛ ተነሳሽነቱ የሆነው ብሔራዊ የስፖርት ምርምር ኮንፈረንስ አዳዲስ ግኝቶች የሚጋሩበት፣ ለክርክር የሚቀርቡበት እና የሚወደሱበት ደማቅ የእውቀት ልውውጥ መድረክ ሆኖ ያገለግላል። ይህ ዓመታዊ ዝግጅት ፈጠራን በማስተባበር እና ንቁ የስፖርት ምርምር ማኅበረሰብ የማዳበር ሥራን በመምራት አካዳሚው የሚጫወተውን ሚና አጉልቶ ያሳያል።

ልህቀትን ወደፊት የሚያራምዱ ግብዓቶች

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በስፖርት ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎችን እና ባለድርሻ አካላትን ለማጎልበት በንቃት በመንቀሳቀስ ከምርምር ባሻገር የሆኑ ሥራዎችን ይሠራል። ከስትራቴጂካዊ ግቦቹ ጋር የሚጣጣሙ ምርምሮችን በገንዘብ በመደገፍ የኢትዮጵያ የስፖርት መልከዓ ምድር ላይ ለውጥ ማምጣት ለሚችሉ ትርጉም ያላቸው ምርምሮች በር ይከፍታል። እጅግ ዘመናዊ የሳይንስ ቤተ ሙከራዎች፣ የተራቀቁ የመረጃ ማከማቻዎች እና ተወዳዳሪ የሌለው የግብዓቶች ተደራሽነት ያለው ይህ አካዳሚ ስኬታማ ለመሆን አስፈላጊ የሆኑትን መሣሪያዎች ለተመራማሪዎች እና ባለሙያዎች ያቀርባል።

በኢትዮጵያ የስፖርትን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በስትራቴጂካዊ ተነሳሽነቶቹ አማካኝነት በመላዋ ኢትዮጵያ ፖሊሲ አወጣጥ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር፣ የአትሌት አፈጻጸምን ለማሻሻል እና የስፖርት ዘርፍ አሠራሮችን ለማዘመን ያልማል። በስፖርት ሳይንስ አዳዲስ ግኝቶችን እውን ለማድረግ ባለው ቁርጠኝነት የሀገሪቷ አትሌቶች፣ አሠልጣኞች እና አስተዳዳሪዎች በዓለም አቀፍ መድረክ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን እውቀት እና መሣሪያዎች ማግኘታቸውን ያረጋግጣል።

በምርምር፣ በፈጠራ እና በትብብር አማካኝነት ስፖርት ላይ ሰፊ ለውጥ ለማምጣት በያዘው ተልዕኮ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚን ይቀላቀሉ። የኢትዮጵያ ስፖርት አዲስ የልህቀት ደረጃዎች ላይ የሚደርስበትን የወደፊት ዘመን አብረን እየቀረጽን ነው።