ዕትመቶች

የግንኙነቶች ክፍል ህትመቶች፦ ስኬቶችን ማስተዋወቅ እና ተሳትፎን ማበረታታት

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የግንኙነቶች ክፍል የአካዳሚውን ራዕይ፣ ስኬቶች እና ፕሮግራሞች ለተለያዩ ሰዎች በማጋራት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ይህ ክፍል በጥንቃቄ በተደራጁ ህትመቶቹ በኩል አትሌቶች፣ ተመራማሪዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና ሰፊው ሕዝብ በአካዳሚው የተያዙ ተነሳሽነቶች ዙሪያ ግንዛቤ ያላቸው እና ተሳትፎ የሚያደርጉ መሆኑን ያረጋግጣል።

ዓመታዊ መጽሔት፦ ታላላቅ ስኬቶችን እና የላቁ ውጤቶችን መዘከር  

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዓመታዊ መጽሔት አካዳሚው በዓመቱ ያሳለፋቸውን ጉልህ ስኬቶች፣ የማይረሱ ክስተቶች እና መንፈስን የሚያነሳሱ ታሪኮች የሚያሳይ ዓመታዊ ህትመት ነው። እንደ የምርምር ግኝቶች፣ የስኬታማ አትሌት ታሪኮች እና ወቅታዊ የፕሮግራም መረጃዎች የመሳሰሉ ልዩ ልዩ ቁልፍ ነገሮችን የሚያካትተው ይህ የዓመት መጽሐፍ አካዳሚው ለልህቀት ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል። ከደማቅ ምስሎች፣ በዝርዝር መረጃ የተሞሉ መጣጥፎች እና ከልብ የመነጩ የአመራር መልዕክቶች ጋር ለስፖርት ማኅበረሰቡ የስኬት መዝገብ እና የተነሳሽነት ምንጭ ሆኖ ያገለግላል።

የመረጃ ብሮሹሮች፦ ከአካዳሚው ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለእርስዎ የሚያቀርብ  

የክፍሉ የመረጃ ብሮሹሮች የአካዳሚውን ፕሮግራሞች፣ መገልገያዎች እና አገልግሎቶች የሚመለከቱ አጠር ያሉ እና በቀላሉ የሚገኙ ማጠቃለያዎችን ያቀርባሉ። ለተለያዩ አንባቢዎች የተቀረጹት እነኚህ ብሮሹሮች እንደ የምርምር እና ፈጠራ ፕሮግራሞች፣ ለአትሌቶች እና አሰልጣኞች የሚቀርቡ የስልጠና እና የእድገት እድሎች፣ እንደ የስፖርት ሳይንስ ቤተ ሙከራዎች እና የመረጃ ማከማቻዎች ያሉ ተደራሽነት ያላቸው ግብዓቶች፣ ከሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የሚደረጉ አጋርነቶች እና ትብብሮች የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናሉ።

እነዚህ ብሮሹሮች በዝግጅቶች፣ ኮንፈረንሶች እና የማኅበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ላይ የሚሰራጩ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል አካዳሚው ለኢትዮጵያ የስፖርት ሥነ-ምህዳር እንዴት አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት በግልጽ መረዳቱን ያረጋግጣሉ።  

የዜና መጽሔቶች፦ ለማኅበረሰቡ ወቅታዊ መረጃ ማድረስ  

በየጊዜው የሚታተሙ የዜና መጽሔቶች አዳዲስ ዜናዎችን፣ መጪ ዝግጅቶችን እና ቁልፍ ማስታወቂያዎችን የሚመልከቱ መረጃዎች ለአካዳሚው ማኅበረሰብ ያደርሳሉ። የምርምር ፕሮጀክቶች፣ የስልጠና ካምፖች እና የስኬት ታሪኮች ዙሪያ አዳዲስ ዜናዎችን የሚያካትተው የዜና መጽሔት ባለድርሻ አካላት ዘንድ የግንኙነት እና የተሳትፎ ስሜትን ያዳብራል።

ልዩ ሪፖርቶች እና አንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ ዕትመቶች  

የግንኙነቶች ክፍል በየጊዜው ከሚያሳትማቸው ጽሑፎች በተጨማሪ አሳሳቢ ጉዳዮችን ለመፍታት ወይም ልዩ ክስተቶችን ለማክበር ልዩ ሪፖርቶች እና አንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ ህትመቶች ሊለቅ ይችላል። እነዚህም የምርምር ግኝት ሪፖርቶችን፣ በስፖርት አስተዳደር ውስጥ ያሉ ምርጥ አሠራሮችን እና ከብሔራዊ ወይም ዓለም አቀፍ ዝግጅቶች ጋር የሚዛመዱ ህትመቶን ያካትታሉ።  

ዲጂታል ተደራሽነት 

የተደራሽነትን አስፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህ ህትመቶች በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ድር-ጣቢያ እና የማኅበራዊ ሚዲያ ቻናሎች በኩል ይቀርባሉ። ይህ ዲጂታል አቀራረብ ሰፋ ያለ አንባቢ ዘንድ መድረስ መቻላቸውን የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ አካዳሚው ለዘመናዊነት እና አካታችነት ካለው ቁርጠኝነት ጋር ይዛመዳል።  

የግንኙነቶች ክፍል በእነዚህ ህትመቶች በኩል የአካዳሚውን ድምጽ ያጎላል፣ የምርት ስሙን ያጠናክራል እንዲሁም በኢትዮጵያ ስፖርት የጋራ የልህቀት ራዕይን ያጎለብታል።

የኢ.ስ.አ (ESA) እ.ኤ.አ 2023 ዓ.ም ዓመታዊ መጽሔት

The የኢ.ስ.አ (ESA) እ.ኤ.አ 2023 ዓ.ም ዓመታዊ መጽሔት እ.ኤ.አ 2023 ዓ.ም የታተመው የኢ.ስ.አ ዓመታዊ መጽሔት በዚያ አስደናቂ ዓመት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ያሳለፈውን ጉዞ የሚያስታውስ ማራኪ ታሪክ ይተርካል። በደማቅ ምስሎች፣ አስደናቂ ትርክቶች እና ጥልቅ የስኬት መግለጫዎች የተሞላው ይህ የዓመት መጽሐፍ አካዳሚው የስፖርት ሳይንስን ለማሳደግ፣ ተሰጥዖን ለማዳበር እና ፈጠራን ለማጎልበት ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚመሰክር ነው...