የብስክሌት ዲፓርትመንት ጠንካራ እና ተወዳዳሪ ብስክሌተኞችን ለማፍራት የኢትዮጵያን ልዩ ልዩ መልከዓ ምድሮች ጥቅም ላይ ያውላል። የብርታት እና የፍጥነት ሥልጠናዎችን በመጠቀም አትሌቶች በከፍተኛ ደረጃ እሽቅድምድሞች ውስጥ ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን ጽናት እና ጥንካሬ ይጎናጸፋሉ። ይህ ዲፓርትመንት ቴክኒካዊ የቭስክሌት ክህሎቶችንም በማስተማር አትሌቶች አፈጻጸማቸውን እያሻሻሉ የተለያዩ መልከዓ ምድሮች ላይ መንዳት እንዲችሉ ያዘጋጃል። እጅግ ዘመናዊ መሣሪያዎች እና የተራቀቁ የስልጠና መገልገያዎች አትሌቶች ለስኬት የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ ያቀርባሉ። የብስክሌት ዲፓርትመንት አትሌቶችን ለኦሎምፒክ ውድድር ጨምሮ ለተለያዩ አካባቢያዊ፣ ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ማዘጋጀት ላይ ጥብቅ ትኩረት በማድረግ የዓለም መድረክ ላይ ውጤት ለማምጣት ዝግጁ የሆኑ የቀጣዩን ትውልድ የኢትዮጵያ የብስክሌት ሻምፒዮኖች የማፍራት ሥራን እየመራ ይገኛል።