የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መሠረት ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በረጅም ርቀት ሩጫ እና በትራክ እና መስክ ውድድሮች ያላትን ታላቅ ታሪክ በኩራት ወደፊት ያራምዳል። በተራቀቁ የስልጠና ስልቶች ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አፈጻጸምን ለማሻሻል እና የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስ ዘመናዊ የስፖርት ሳይንሶችን ይጠቀማል። የተሰጥዖ ልየታ ሥራ ቀደም ብሎ የሚጀምር ሲሆን፣ ይህም ጥሩ ተስፋ ያላቸው አትሌቶች በግለሰብ ደረጃ የተቀረጸ ሥልጠና እና እድገት ማግኘታቸውን ያረጋግጣል። የአትሌቶክስ ዲፓርትመንቱ እንደ ኦሎምፒክስ እና የዓለም ሻምፒዮና ላሉ ታዋቂ ውድድሮች አትሌቶችን ማዘጋጀት ላይ በማተኮር ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ እየወከሉ የሚገኙ በርካታ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶችን ያፈራ በመሆኑ፣ በአትሌቲክስ ዘርፍ ስመጥር ተቋም መሆኑን አረጋግጧል።