አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 3፡00 - 11:00
info@esacademy.gov.et |

የቦክስ ዲፓርትመንት

የቦክስ ዲፓርትመንት አካላዊ ብርታትን ከቴክኒካዊ ብቃት እና አዕምሯዊ ጥንካሬ ጋር የሚያዋህዱ አትሌቶችን ለመገንባት ይሠራል። በጥብቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሞች አማካኝነት አትሌቶች የቦክስ ሪንግ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን ብርታት እና ጥንካሬ ያዳብራሉ። ዲፓርትመንቱ እንደ የእግር ሥራ፣ የመከላከል ክህሎት እና የቡጢ አሰነዛዘር የመሳሰሉ ቁልፍ ቴክኒኮችን በማዳበር ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ በውድድር ውስጥም ለስፖርታዊ ጨዋነት፣ ዲሲፕሊን እና ሥነ-ምግባር ወሳኝነትን አጽንዖት ይሰጣል። አትሌቶችን ለብሔራዊ እና ዓለም አቀፍ የቦክሲንግ ውድድሮች የሚያዘጋጀው የቦክሲንግ ዲፓርትመንት አትሌቶች በሪንግ ውስጥ እና ከዚያም ባሻገር ስኬታማ ለመሆን ብቁ መሆናቸውን በማረጋገጥ በስፖርቱ ውስጥ የባለሙያነት እና የደኅንነት ባህልን ያጎለብታል።

Related Post

የዋና ዲፓርትመንትየዋና ዲፓርትመንት

የዋና ዲፓርትመንት ልዩ ቴክኒካዊ ብቃት፣ ብርታት እና የውድድር መንፈስ የተላበሱ አትሌቶችን ለማፍራት የተቋቋመ ነው። ውሃ መቅዘፍ፣ አዟዟር እና አጀማመርን በማዳበር ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውኃ ውስጥ የላቀ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ ይረዳል። የጥንካሬ እና የአካል ብቃት ፕሮግራሞች የዋና ውድድር ውስጥ ስኬታማ ለመሆን

የአትሌቲክስ ዲፓርትመንትየአትሌቲክስ ዲፓርትመንት

የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መሠረት ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በረጅም ርቀት ሩጫ እና በትራክ እና መስክ ውድድሮች ያላትን ታላቅ ታሪክ በኩራት ወደፊት ያራምዳል። በተራቀቁ የስልጠና ስልቶች ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አፈጻጸምን ለማሻሻል እና የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስ ዘመናዊ የስፖርት ሳይንሶችን

የጠረንጴዛ ቴኒስ ዲፓርትመንትየጠረንጴዛ ቴኒስ ዲፓርትመንት

የጠረጴዛ ቴኒስ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውስጥ ትኩረት፣ ቅልጥፍና እና ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብን በማዳበር እጅግ አጣዳፊ ከሚባሉት መካከል አንዱ በሆነው ስፖርት ውስጥ ስኬታማ መሆን እንዲችሉ ይረዳል። የዲፓርትመንቱ ስልታዊ የስልጠና ፕሮግራም ፈጣን ምላሽ የመስጠት ችሎታን፣ የእጅ እና ዓይን ቅንጅትን እና እንደ ቆረጣ፣ ሰርቭ እና የእግር ሥራ የመሳሰሉ የተራቀቁ ቴክኒኮችን ያዳብራል። አትሌቶች ከቴክኒካዊ ክህሎቶች በተጨማሪ

amአማርኛ