የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአካዳሚው አስተዳደር

የአካዳሚው አስተዳደር

አመራሮቻችንን ይተዋወቁ

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ
ዋና ዳይሬክተር
አቶ አምበሳው እንየው

አቶ አምበሳው የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚን ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ እና አጠቃላይ አስተዳደር በመቆጣጠር የላቁ አትሌቶች እና ባለሙያዎች የማፍራት ተልዕኮው ስኬታማ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ይህ ሚና አጋርነቶችን ማጎልበት፣ ፈጠራን ማበረታታት እና አካዳሚው በስፖርት ልህቀት በሀገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ሆኖ መቀጠሉን ማረጋገጥን ያካትታል።

የስልጠና እና ውድድር
ምክትል ዋና ዳይሬክተር
አቶ ደሳለኝ በላዬ

አቶ ደሳለኝ በላዬ የአካዳሚውን የስልጠና ፕሮግራሞች እና የውድድር ዝግጅቶች ዲዛይን እና ትግበራ ያስተዳድራሉ። ይህ ጽሕፈት ቤት አትሌቶችን ለብሔራዊ እና ዓለም አቀፍ ስኬት ለማዘጋጀት ሁለንተናዊ እና ምርምር ላይ የተመሰረቱ ስልጠናዎች ላይ ያተኩራል።

የአስተዳደራዊ ልማት
ምክትል ዋና ዳይሬክተር
ዶ/ር ፍቃዱ መኩሪያ

የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፊቃዱ የአካዳሚውን አሠራር እና መሠረተ ልማታዊ ገጽታ ይቆጣጠራሉ። ቁልፍ ሚናዎቻቸው የግብዓት አጠቃቀም አግባብ ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣ መገልገያዎችን ማሻሻል እና የአካዳሚውን እድገት እና ዘላቂነት መደገፍን ያካትታሉ።

የጥናት እና ምርምር
ምክትል ዋና ዳይሬክተር
ዶ/ር

ዶ/ር የስፖርት ሳይንስ፣ የአትሌት አቅም ጉልበታ እና ስልጠና አሰጣጥን ለማሻሻል የተጀመሩ ተነሳሽነቶችን እያስተዳደሩ ይገኛሉ። በመረጃ የተደገፉ ፕሮጀክቶችን እና ስትራቴጂካዊ አጋርነቶችን አዳብሮ ፈጠራን በማጎልበት አካዳሚው በሀገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖረውን ተጽዕኖ እያጠናከሩም ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ስፖርት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለያዝነው ተልዕኮ የአመራር ቡድናችን የጀርባ አጥንት ነው። በከፍተኛ ልምድ እና ለፈጠራ ባለው ቁርጠኝነት አማካኝነት ይህ ቡድን አካዳሚው በስፖርት ልማት የልህቀት ተምሳሌት እና ዓለም አቀፍ መሪ ሆኖ መቀጠሉን ያረጋግጣል።