አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 3፡00 - 11:00
info@esacademy.gov.et |

ዲፓርትመንቶች

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እያንዳንዳቸው ተሰጥዖን ለመለየት፣ ለማዳበር እና ለማሳደግ በጥንቃቄ የተቀረጹ የሚኮራባቸው 10 ልዩ የስፖርት ዲፓርትመንቶች አሉት። እነዚህ ዲፓርትመንቶች የልህቀት ምሰሶ ሆነው በመቆም በብሔራዊም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረኮች ስኬታማ እንዲሆኑ አትሌቶችን የሚያዘጋጁ የተጠኑ የስልጠና ፕሮግራሞችን ያቀርባሉ።

አካዳሚው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በሆኑ ዘመናዊ መገልገያዎቹ፣ ከፍተኛ ክህሎት ባላቸው አሰልጣኞች በተዋቀረው ቡድኑ እና ለሁለንተናዊ እድገት ባለው ቁርጠኝነት እያንዳንዱ አትሌት አካላዊ ስልጠና ማግኘቱን ብቻ ሳይሆን አዕምሯዊ ዝግጁነት ያለው እና በሥነ-ምግባር የታነጸ መሆኑን ያረጋግጣል።ይህ ሁለገብ አቀራረብ አትሌቶቻችን በሙያቸው ዘላቂ ስኬት ለማግኘት ወሳኝ የሆኑትን የዲሲፕሊን፣ የብርታት እና የስፖርታዊ ጨዋነት እሴቶች እንዲላበሱ ያስችላል።

እያንዳንዱ ዲፓርትመንት ለአካዳሚው ተልዕኮ ልዩ አስተዋጽዖ የሚያበረክት ሲሆን፣ በየራሳቸው ዲሲፕሊኖች ውስጥ መሠረታዊ ክህሎቶችን በማዳበር፣ የቡድን ሥራን በማጎልበት እና ፈጠራን በማበረታታት ላይ ያተኩራሉ። ከአትሌቲክስ ዲፓርትመንቱ ጥብቅ የብርታት ስልጠና ጀምሮ በጠረጴዛ ቴኒስ እስከሚዳብረው ትኩረት እና ቅልጥፍና ድረስ እያንዳንዱ ፕሮግራም አዲስ አድማሶችን ለመፍጠር እና ልህቀትን ወደፊት ለመግፋት የተቀረጸ ነው።

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የስልጠና ተቋም ብቻ አይደለም፤ የተነሳሽነት እና የለውጥ ማዕከል ነው። በእነዚህ 10 ልዩ ዲፓርትመንቶች አማካኝነት የኢትዮጵያን ሰፊ የአትሌቲክስ ትሩፋት እየጠበቅን ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ ትውልድ ድል አድራጊዎችም አዳዲስ በሮችን እየከፈትን ነው። የአካዳሚው ፕሮግራሞች ለብሔራዊ ውድድሮችም ሆነ ለዓለም አቀፍ መድረኮች በሚደረጉ ዝግጅቶች ውስጥ በዓለም መድረክ የላቀ ውጤት ለማምጣት አትሌቶችን በሚያስፈልጋቸው ክህሎት፣ በራስ መተማመን እና ቁርጠኝነት ያስታጥቃሉ።

ዲፓርትመንቶች
የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት

የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መሠረት ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በረጅም ርቀት ሩጫ እና በትራክ እና መስክ ውድድሮች ያላትን ታላቅ ታሪክ በኩራት ወደፊት ያራምዳል። በተራቀቁ የስልጠና ስልቶች ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አፈጻጸምን ለማሻሻል እና የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስ ዘመናዊ የስፖርት ሳይንሶችን

ዲፓርትመንቶች
የቅርጫት ኳስ ዲፓርትመንት

የቅርጫት ኳስ ዲፓርትመንት ከፍተኛ ቅልጥፍና እና ጉልበት በሚጠይቀው የቅርጫት ኳስ ጨዋታ የተካኑ አትሌቶችን ለመፍጠር ሥልጠና ይሰጣል። አትሌቶች በቴክኒካዊ እና ስትራቴጂካዊ ሥልጠና አማካኝነት የማጥቃት እና የመከላከል ጨዋታዎችን ውስብስብነት፣ የኳስ አያያዝ እና ጎል የማስቆጠር ቴክኒኮችን ይማራሉ። ዲፓርትመንቱ ቁልፍ አካላዊ ክህሎቶችን በማዳበር ላይም

ዲፓርትመንቶች
የቦክስ ዲፓርትመንት

የቦክስ ዲፓርትመንት አካላዊ ብርታትን ከቴክኒካዊ ብቃት እና አዕምሯዊ ጥንካሬ ጋር የሚያዋህዱ አትሌቶችን ለመገንባት ይሠራል። በጥብቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሞች አማካኝነት አትሌቶች የቦክስ ሪንግ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን ብርታት እና ጥንካሬ ያዳብራሉ። ዲፓርትመንቱ እንደ የእግር ሥራ፣ የመከላከል ክህሎት እና የቡጢ አሰነዛዘር

ዲፓርትመንቶች
የብስክሌት ዲፓርትመንት

የብስክሌት ዲፓርትመንት ጠንካራ እና ተወዳዳሪ ብስክሌተኞችን ለማፍራት የኢትዮጵያን ልዩ ልዩ መልከዓ ምድሮች ጥቅም ላይ ያውላል። የብርታት እና የፍጥነት ሥልጠናዎችን በመጠቀም አትሌቶች በከፍተኛ ደረጃ እሽቅድምድሞች ውስጥ ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን ጽናት እና ጥንካሬ ይጎናጸፋሉ። ይህ ዲፓርትመንት ቴክኒካዊ የብስክሌት ክህሎቶችንም

ዲፓርትመንቶች
የእግር ኳስ ዲፓርትመንት

የእግር ኳስ ዲፓርትመንት የሥነ-ምግባር፣ የቡድን ሥራ እና የጥንካሬ ተምሳሌት የሆኑ ከፍተኛ ችሎታ እና ቴክኒካዊ ብልሃት ያላቸው ተጫዋቾችን ለማፍራት ተግቶ ይሠራል። ይህ ዲፓርትመንት እንደ ቴክኒካዊ ክህሎቶች፣ ቴክኒካዊ ግንዛቤ እና አካላዊ ብቃት የመሳሰሉ ወሳኝ መስኮችን የሚሸፍን ሁሉን አቀፍ የስልጠና መርሃ ግብር ያቀርባል። ሜዳ ላይ ከሚደረግ ሥልጠና ጎን ለጎን

ዲፓርትመንቶች
የዋና ዲፓርትመንት

የዋና ዲፓርትመንት ልዩ ቴክኒካዊ ብቃት፣ ብርታት እና የውድድር መንፈስ የተላበሱ አትሌቶችን ለማፍራት የተቋቋመ ነው። ውሃ መቅዘፍ፣ አዟዟር እና አጀማመርን በማዳበር ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውኃ ውስጥ የላቀ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ ይረዳል። የጥንካሬ እና የአካል ብቃት ፕሮግራሞች የዋና ውድድር ውስጥ ስኬታማ ለመሆን

ዲፓርትመንቶች
የጠሬንጴዛ ዲፓርትመንት

የጠረጴዛ ቴኒስ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውስጥ ትኩረት፣ ቅልጥፍና እና ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብን በማዳበር እጅግ አጣዳፊ ከሚባሉት መካከል አንዱ በሆነው ስፖርት ውስጥ ስኬታማ መሆን እንዲችሉ ይረዳል። የዲፓርትመንቱ ስልታዊ የስልጠና ፕሮግራም ፈጣን ምላሽ የመስጠት ችሎታን፣ የእጅ እና ዓይን ቅንጅትን እና እንደ ቆረጣ፣ ሰርቭ እና የእግር ሥራ የመሳሰሉ የተራቀቁ ቴክኒኮችን ያዳብራል። አትሌቶች ከቴክኒካዊ ክህሎቶች በተጨማሪ

ዲፓርትመንቶች
የመረብ ኳስ ዲፓርትመንት

የመረብ ኳስ ዲፓርትመንት በቤት ውስጥ እና የባህር ዳርቻ መረብ ኳስ ጨዋታዎች ሁለገብ ስልጠናዎችን በማቅረብ አትሌቶችን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ከሚታይባቸው የዓለም ስፖርት መካከል አንዱ በሆነው መረብ ኳስ ለስኬት ያዘጋጃል። ስልጠናው እንደ ሰርቭ፣ ብሎክ እና የመከላከል ቴክኒኮች በመሳሰሉ ወሳኝ ክህሎቶች ላይ ያተኩራል። ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶች ሜዳ ላይ ያለምንም ችግር እንደ አንድ ሆነው መሥራት መቻላቸውን ለማረጋገጥ

ዲፓርትመንቶች
የወርልድ ቴክዋንዶ ዲፓርትመንት

የወርልድ ቴኳንዶ ዲፓርትመንት የቴኳንዶን አካላዊ ቅልጥፍና ከአዕምሯዊ ጥንካሬ ጋር በማቀናጀት ሁለገብ አትሌቶችን ለመፍጠር ይሠራል። የስፓሪንግ ቴክኒኮችን፣ ራስን የመከላከል ስትራቴጂዎችን እና ፓተርኖችን ማዳበር ላይ በማተኮር አትሌቶች አካላዊ እና አዕምሯዊ ጥንካሬያቸውን የሚያጎለብቱበት ጥብቅ ስልጠና ያገኛሉ። ዲፓርትመንቱ እንደ ክብር፣ ትኩረት ኣና ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብ ያሉ እሴቶችን በማስረጽ የመልካም ባህሪ ግንባታ ላይ ጠንካራ አጽንዖት ይሰጣል። አትሌቶች በሚያገኙት የጥንካሬ እና የመለጠጥ ስልጠናዎች ተደግፈው

ያገኘናቸው ሽልማቶች

amአማርኛ