አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 3፡00 - 11:00
info@esacademy.gov.et |
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዲፓርትመንቶች የጠረንጴዛ ቴኒስ ዲፓርትመንት

የጠረንጴዛ ቴኒስ ዲፓርትመንት

የጠረጴዛ ቴኒስ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውስጥ ትኩረት፣ ቅልጥፍና እና ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብን በማዳበር እጅግ አጣዳፊ ከሚባሉት መካከል አንዱ በሆነው ስፖርት ውስጥ ስኬታማ መሆን እንዲችሉ ይረዳል። የዲፓርትመንቱ ስልታዊ የስልጠና ፕሮግራም ፈጣን ምላሽ የመስጠት ችሎታን፣ የእጅ እና ዓይን ቅንጅትን እና እንደ ቆረጣ፣ ሰርቭ እና የእግር ሥራ የመሳሰሉ የተራቀቁ ቴክኒኮችን ያዳብራል። አትሌቶች ከቴክኒካዊ ክህሎቶች በተጨማሪ ውድድሮች ላይ የተቀናቃኛቸውን ስትራቴጂ በመገመት የስፖርቱ ወሳኝ ገጽታ የሆነውን እንደ ሁኔታው ተለዋዋጭ የመሆን ችሎታን ይማራሉ። ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶችን ለብሔራዊ እና ዓለም አቀፍ የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድሮች በማዘጋጀት በዚህ ከፍተኛ ተወዳዳሪነት በሚታይበት ስፖርት ውስጥ የኢትዮጵያን ስም ከፍ ለማድረግ ዓልሞ እየሠራ በሀገሪቷ እያደጉ ለሚገኙት ተወዳዳሪ አትሌቶች ዓለም አቀፍ እውቅናን ያስገኛል።

Related Post

የቅርጫት ኳስ ዲፓርትመንትየቅርጫት ኳስ ዲፓርትመንት

የቅርጫት ኳስ ዲፓርትመንት ከፍተኛ ቅልጥፍና እና ጉልበት በሚጠይቀው የቅርጫት ኳስ ጨዋታ የተካኑ አትሌቶችን ለመፍጠር ሥልጠና ይሰጣል። አትሌቶች በቴክኒካዊ እና ስትራቴጂካዊ ሥልጠና አማካኝነት የማጥቃት እና የመከላከል ጨዋታዎችን ውስብስብነት፣ የኳስ አያያዝ እና ጎል የማስቆጠር ቴክኒኮችን ይማራሉ። ዲፓርትመንቱ ቁልፍ አካላዊ ክህሎቶችን በማዳበር ላይም

የወርልድ ቴክዋንዶ ዲፓርትመንትየወርልድ ቴክዋንዶ ዲፓርትመንት

የወርልድ ቴኳንዶ ዲፓርትመንት የቴኳንዶን አካላዊ ቅልጥፍና ከአዕምሯዊ ጥንካሬ ጋር በማቀናጀት ሁለገብ አትሌቶችን ለመፍጠር ይሠራል። የስፓሪንግ ቴክኒኮችን፣ ራስን የመከላከል ስትራቴጂዎችን እና ፓተርኖችን ማዳበር ላይ በማተኮር አትሌቶች አካላዊ እና አዕምሯዊ ጥንካሬያቸውን የሚያጎለብቱበት ጥብቅ ስልጠና ያገኛሉ። ዲፓርትመንቱ እንደ ክብር፣ ትኩረት ኣና ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብ ያሉ እሴቶችን በማስረጽ የመልካም ባህሪ ግንባታ ላይ ጠንካራ አጽንዖት ይሰጣል። አትሌቶች በሚያገኙት የጥንካሬ እና የመለጠጥ ስልጠናዎች ተደግፈው

የዋና ዲፓርትመንትየዋና ዲፓርትመንት

የዋና ዲፓርትመንት ልዩ ቴክኒካዊ ብቃት፣ ብርታት እና የውድድር መንፈስ የተላበሱ አትሌቶችን ለማፍራት የተቋቋመ ነው። ውሃ መቅዘፍ፣ አዟዟር እና አጀማመርን በማዳበር ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውኃ ውስጥ የላቀ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ ይረዳል። የጥንካሬ እና የአካል ብቃት ፕሮግራሞች የዋና ውድድር ውስጥ ስኬታማ ለመሆን

amአማርኛ