አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 3፡00 - 11:00
info@esacademy.gov.et |

የዋና ዲፓርትመንት

የዋና ዲፓርትመንት ልዩ ቴክኒካዊ ብቃት፣ ብርታት እና የውድድር መንፈስ የተላበሱ አትሌቶችን ለማፍራት የተቋቋመ ነው። ውሃ መቅዘፍ፣ አዟዟር እና አጀማመርን በማዳበር ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውኃ ውስጥ የላቀ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ ይረዳል። የጥንካሬ እና የአካል ብቃት ፕሮግራሞች የዋና ውድድር ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልገውን ብርታት የሚገነቡ ሲሆን፣ የኦሎምፒክ ስታንዳርድ መዋኛ ገንዳዎች እና የስልጠና መሣሪያዎች ተደራሽነት ደግሞ አትሌቶች ዘመናዊ በሆነ ሁኔታ መሰልጠናቸውን ያረጋግጣሉ። ዋናተኞችን ከሀገር ውስጥ ውድድሮች ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ መድረኮች ድረስ ባሉ የተለያዩ ደረጃዎች እንዲወዳደሩ የሚያዘጋጀው የዋና ዲፓርትመንት በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን አሸናፊም በመሆን ለኢትዮጵያ ኩራት የሚሆኑ አትሌቶችን ለማፍራት ያልማል።

Related Post

የመረብ ኳስ ዲፓርትመንትየመረብ ኳስ ዲፓርትመንት

የመረብ ኳስ ዲፓርትመንት በቤት ውስጥ እና የባህር ዳርቻ መረብ ኳስ ጨዋታዎች ሁለገብ ስልጠናዎችን በማቅረብ አትሌቶችን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ከሚታይባቸው የዓለም ስፖርት መካከል አንዱ በሆነው መረብ ኳስ ለስኬት ያዘጋጃል። ስልጠናው እንደ ሰርቭ፣ ብሎክ እና የመከላከል ቴክኒኮች በመሳሰሉ ወሳኝ ክህሎቶች ላይ ያተኩራል። ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶች ሜዳ ላይ ያለምንም ችግር እንደ አንድ ሆነው መሥራት መቻላቸውን ለማረጋገጥ

የአትሌቲክስ ዲፓርትመንትየአትሌቲክስ ዲፓርትመንት

የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መሠረት ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በረጅም ርቀት ሩጫ እና በትራክ እና መስክ ውድድሮች ያላትን ታላቅ ታሪክ በኩራት ወደፊት ያራምዳል። በተራቀቁ የስልጠና ስልቶች ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አፈጻጸምን ለማሻሻል እና የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስ ዘመናዊ የስፖርት ሳይንሶችን

የቦክስ ዲፓርትመንትየቦክስ ዲፓርትመንት

የቦክስ ዲፓርትመንት አካላዊ ብርታትን ከቴክኒካዊ ብቃት እና አዕምሯዊ ጥንካሬ ጋር የሚያዋህዱ አትሌቶችን ለመገንባት ይሠራል። በጥብቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሞች አማካኝነት አትሌቶች የቦክስ ሪንግ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን ብርታት እና ጥንካሬ ያዳብራሉ። ዲፓርትመንቱ እንደ የእግር ሥራ፣ የመከላከል ክህሎት እና የቡጢ አሰነዛዘር

amአማርኛ