አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 3፡00 - 11:00
info@esacademy.gov.et |

የእግር ኳስ ዲፓርትመንት

የእግር ኳስ ዲፓርትመንት የሥነ-ምግባር፣ የቡድን ሥራ እና የጥንካሬ ተምሳሌት የሆኑ ከፍተኛ ችሎታ እና ቴክኒካዊ ብልሃት ያላቸው ተጫዋቾችን ለማፍራት ተግቶ ይሠራል። ይህ ዲፓርትመንት እንደ ቴክኒካዊ ክህሎቶች፣ ቴክኒካዊ ግንዛቤ እና አካላዊ ብቃት የመሳሰሉ ወሳኝ መስኮችን የሚሸፍን ሁሉን አቀፍ የስልጠና መርሃ ግብር ያቀርባል። ሜዳ ላይ ከሚደረግ ሥልጠና ጎን ለጎን ጠንካራ የአመራር እና የቡድን ሥራ እሴቶች ውስጥ በማስረጽ በውድድር ሁኔታ ውስጥ ስኬታማ መሆን እንዲችሉ ያጎለብታል። ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶችን ለሀገር ውስጥ ሊጎች እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚያዘጋጅ ሲሆን፣ በእግር ኳስ ትምህርት እና የኑሮ ክህሎቶች ሥልጠና አማካኝነት የወጣቶች ተስትፎንም ያዳብራል። የእግር ኳስ ዲፓርትመንት በከፍተኛ ደረጃ በሚገኙ ክለቦችም ሆነ በብሔራዊ ቡድኖች ውስጥ ስኬታማ የሚሆኑ ተጫዋቾችን በማፍራት በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ውስጥ የኢትዮጵያን ደረጃ ከፍ ለማድረግ ዓልሞ ይሠራል።

Related Post

የመረብ ኳስ ዲፓርትመንትየመረብ ኳስ ዲፓርትመንት

የመረብ ኳስ ዲፓርትመንት በቤት ውስጥ እና የባህር ዳርቻ መረብ ኳስ ጨዋታዎች ሁለገብ ስልጠናዎችን በማቅረብ አትሌቶችን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ከሚታይባቸው የዓለም ስፖርት መካከል አንዱ በሆነው መረብ ኳስ ለስኬት ያዘጋጃል። ስልጠናው እንደ ሰርቭ፣ ብሎክ እና የመከላከል ቴክኒኮች በመሳሰሉ ወሳኝ ክህሎቶች ላይ ያተኩራል። ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶች ሜዳ ላይ ያለምንም ችግር እንደ አንድ ሆነው መሥራት መቻላቸውን ለማረጋገጥ

የወርልድ ቴክዋንዶ ዲፓርትመንትየወርልድ ቴክዋንዶ ዲፓርትመንት

የወርልድ ቴኳንዶ ዲፓርትመንት የቴኳንዶን አካላዊ ቅልጥፍና ከአዕምሯዊ ጥንካሬ ጋር በማቀናጀት ሁለገብ አትሌቶችን ለመፍጠር ይሠራል። የስፓሪንግ ቴክኒኮችን፣ ራስን የመከላከል ስትራቴጂዎችን እና ፓተርኖችን ማዳበር ላይ በማተኮር አትሌቶች አካላዊ እና አዕምሯዊ ጥንካሬያቸውን የሚያጎለብቱበት ጥብቅ ስልጠና ያገኛሉ። ዲፓርትመንቱ እንደ ክብር፣ ትኩረት ኣና ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብ ያሉ እሴቶችን በማስረጽ የመልካም ባህሪ ግንባታ ላይ ጠንካራ አጽንዖት ይሰጣል። አትሌቶች በሚያገኙት የጥንካሬ እና የመለጠጥ ስልጠናዎች ተደግፈው

የዋና ዲፓርትመንትየዋና ዲፓርትመንት

የዋና ዲፓርትመንት ልዩ ቴክኒካዊ ብቃት፣ ብርታት እና የውድድር መንፈስ የተላበሱ አትሌቶችን ለማፍራት የተቋቋመ ነው። ውሃ መቅዘፍ፣ አዟዟር እና አጀማመርን በማዳበር ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውኃ ውስጥ የላቀ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ ይረዳል። የጥንካሬ እና የአካል ብቃት ፕሮግራሞች የዋና ውድድር ውስጥ ስኬታማ ለመሆን

amአማርኛ