አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 3፡00 - 11:00
info@esacademy.gov.et |
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዲፓርትመንቶች የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት

የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት

የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መሠረት ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በረጅም ርቀት ሩጫ እና በትራክ እና መስክ ውድድሮች ያላትን ታላቅ ታሪክ በኩራት ወደፊት ያራምዳል። በተራቀቁ የስልጠና ስልቶች ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አፈጻጸምን ለማሻሻል እና የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስ ዘመናዊ የስፖርት ሳይንሶችን ይጠቀማል። የተሰጥዖ ልየታ ሥራ ቀደም ብሎ የሚጀምር ሲሆን፣ ይህም ጥሩ ተስፋ ያላቸው አትሌቶች በግለሰብ ደረጃ የተቀረጸ ሥልጠና እና እድገት ማግኘታቸውን ያረጋግጣል። የአትሌቶክስ ዲፓርትመንቱ እንደ ኦሎምፒክስ እና የዓለም ሻምፒዮና ላሉ ታዋቂ ውድድሮች አትሌቶችን ማዘጋጀት ላይ በማተኮር ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ እየወከሉ የሚገኙ በርካታ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶችን ያፈራ በመሆኑ፣ በአትሌቲክስ ዘርፍ ስመጥር ተቋም መሆኑን አረጋግጧል።


 

Related Post

የጠረንጴዛ ቴኒስ ዲፓርትመንትየጠረንጴዛ ቴኒስ ዲፓርትመንት

የጠረጴዛ ቴኒስ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውስጥ ትኩረት፣ ቅልጥፍና እና ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብን በማዳበር እጅግ አጣዳፊ ከሚባሉት መካከል አንዱ በሆነው ስፖርት ውስጥ ስኬታማ መሆን እንዲችሉ ይረዳል። የዲፓርትመንቱ ስልታዊ የስልጠና ፕሮግራም ፈጣን ምላሽ የመስጠት ችሎታን፣ የእጅ እና ዓይን ቅንጅትን እና እንደ ቆረጣ፣ ሰርቭ እና የእግር ሥራ የመሳሰሉ የተራቀቁ ቴክኒኮችን ያዳብራል። አትሌቶች ከቴክኒካዊ ክህሎቶች በተጨማሪ

የእግር ኳስ ዲፓርትመንትየእግር ኳስ ዲፓርትመንት

የእግር ኳስ ዲፓርትመንት የሥነ-ምግባር፣ የቡድን ሥራ እና የጥንካሬ ተምሳሌት የሆኑ ከፍተኛ ችሎታ እና ቴክኒካዊ ብልሃት ያላቸው ተጫዋቾችን ለማፍራት ተግቶ ይሠራል። ይህ ዲፓርትመንት እንደ ቴክኒካዊ ክህሎቶች፣ ቴክኒካዊ ግንዛቤ እና አካላዊ ብቃት የመሳሰሉ ወሳኝ መስኮችን የሚሸፍን ሁሉን አቀፍ የስልጠና መርሃ ግብር ያቀርባል። ሜዳ ላይ ከሚደረግ ሥልጠና ጎን ለጎን

የዋና ዲፓርትመንትየዋና ዲፓርትመንት

የዋና ዲፓርትመንት ልዩ ቴክኒካዊ ብቃት፣ ብርታት እና የውድድር መንፈስ የተላበሱ አትሌቶችን ለማፍራት የተቋቋመ ነው። ውሃ መቅዘፍ፣ አዟዟር እና አጀማመርን በማዳበር ላይ የሚያተኩረው ይህ ዲፓርትመንት አትሌቶች ውኃ ውስጥ የላቀ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ ይረዳል። የጥንካሬ እና የአካል ብቃት ፕሮግራሞች የዋና ውድድር ውስጥ ስኬታማ ለመሆን

amአማርኛ