አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 3፡00 - 11:00
info@esacademy.gov.et |
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዜና እና መግለጫዎች አካዳሚው በ8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር መክፈቻ ላይ ፎቶ ኤግዚቢሽን አሳየ

አካዳሚው በ8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር መክፈቻ ላይ ፎቶ ኤግዚቢሽን አሳየ

ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ወላይታ ሶዶ

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋራ በመሆን ባለፉት 6 ተከታታይ አመታት በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ጥር 27/2017 ዓ.ም ለ8ኛ ጊዜ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ወላይታ ሶዶ ከተማ ላይ በደማቅ ስነ-ስርአት የተከፈተ ሲሆን አካዳሚው በመድረኩ በፎቶ ኤግዚቢሽን እና በተለያዩ የኮሙንኬሽን መሳሪያዎች ለስፖርት ቤተሰቡ ስለ አካዳሚው በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት አስተላልፏል።

በመክፈቻ ስነ-ስርአቱ አካዳሚው ከዚህ በፊት በሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ላይ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተመርጠው በክለቦችና በብሄራዊ ቡድን በመመረጥ በአህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ውጤታማ የነበሩ ነባር ሰልጣኞችን በፎቶ ኤግዚብሽን፣በዘጋቢ ፊልም፣ በሚዲያ፣በገለፃ፣ በመጽሄት፣በብሮሸር እና በሌሎች በተለያዩ የኮምኒኬሽን መሳሪያዎች ለስፖርት ቤተሰቡ የአካዳሚውን ውጤታማነት የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል።

በውድድሩ አካዳሚው ለቀጣይ በ2018 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አካዳሚውን የሚቀላቀሉ እጩ ሰልጣኞችን ይመለምላል።

በደማቅ ሁኔታ በተከፈተው 8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ላይ በተለያየ ደረጃ ላይ ያሉ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የአካዳሚው የጥናትና ምርምር እና ማማከር አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አመንሲሳ ከበደ እና አሰልጣኞቸ ተገኝተዋል። የምዘና ውድድሩ ከጥር 27/2017 ዓ.ም እስከ የካቲት 05/2017 ዓ.ም የሚካሂያድ ሲሆን በውድድሩ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ2000 በላይ ታዳጊዎች በ11 የስፖርት አይነቶች ይወዳደራሉ።

Related Post

amአማርኛ