አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 3፡00 - 11:00
info@esacademy.gov.et |
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዜና እና መግለጫዎች አካዳሚው በኢትዮጵያ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ የ1ኛ ዙር ውድድሩን 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ

አካዳሚው በኢትዮጵያ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ የ1ኛ ዙር ውድድሩን 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ

ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በ2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ሲሳተፍ የቆየው የአካዳሚው ከ20 አመት በታች የ4ኛ አመት የሴቶች እግር ኳስ ሰልጣኞች ቡድን የሊጉን የመጨረሻ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታውን ጥር 18/2017 ዓ.ም 10:00 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ሎጊታ አርቴፊሻል ስቴዲየም ጉለሌ ክፍለ ከተማን ገጥሞ 4ለ2 በማሸነፍ የ1ኛ ዙር ውድድሩን 3ኛ ደረጃን በመያዝ በስኬት አጠናቀቀ።

የአካዳሚውን የመጨረሻ ጨዋታ የማሸነፊያ ጎሎች የጨዋታው ኮኮብ የተባለችው ምህረት አየለ ሁለት ጎሎችን ስታስቆጥር ቀሪዎችን ጎሎች ደግሞ ሀና አብርሃም እና አሊያ አማን አስቆጥረዋል።

አካዳሚው በሊጉ በ1ኛ ዙር ካደረጋቸው 13 ጨዋታዎች ትዕግስት ዮሀኒስ ሶስት ጊዜ፣ ቃልኪዳን ዘላለም፣ ማህሌት ሲራክ፣ ረድኤት ክንደ፣ ምህረት አየለ እና ማንጠግቦሽ በ8 ጨዋታዎች ኮኮብ ተጨዋች ማስመረጥ ብሏል።

አካዳሚው በሊጉ ከፍተኛ ድምቀት በመሆን በዙሩ #13_ጨዋታዎችን አድርጎ #ስምንቱን_አሸንፎ #ሶስቱን_አቻ በመለያየት ቀሪውን #ሁለት_ጨዋታ ብቻ ተሸንፎ #27_ነጥቦችን በመሰብሰብ የመጀመሪያውን ዙር ከሽገር ሲቲ እና ከይርጋጨፌ ቡና በመቀጠል #3ኛ_ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ድንቅ ጊዜ አሳልፏል።rd_place behind Sheger City and Yirgachefe Coffee.

የሊጉ የ2ኛ ዙር ውድድር ከጥቂት ረፍት ቆይታ በኃላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያሳውቀው ቦታና ቀን ድርጊት መረሀ ግብር መሰረት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

Related Post

amአማርኛ