አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 3፡00 - 11:00
info@esacademy.gov.et |

ወርልድ ቴክዋንዶ ሻምፒዮና

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ አዳራሽ ኢምፔሪያል፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአትሌቲክስ ልህቀት እና የባህል አንድነት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩበትን ወርልድ ቴኳንዶ ሻምፒዮና ለማስተናገድ ዕድሉን በማግኘቱ በጣም ደስተኛ ነው። ይህ ታላቅ ዝግጅት የስፖርቱን ኃይል፣ ትኩረት እና ዲሲፕሊን በሚያሳዩ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ታላላቅ የቴኳንዶ አትሌቶችን ያሰባስባል። ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው መገልገያዎች እና ደማቅ ድባብ ያለው ይህ ሻምፒዮና የስፖርታዊ ጨዋነት እና የዓለም አቀፍ ትብብር መዘክር መሆኑ አይቀሬ ነው። ታዳሚዎች ከውድድሩ ባሻገር የባህል ኤግዚቢሽኖችን የመጎብኘት፣ በባለሙያዎች የሚመሩ አውደጥናቶች ላይ የመሳተፍ እና ከዓለም አቀፍ አሸናፊዎች ጋር የመተዋወቅ ዕድል ያገኛሉ።

መግቢያ በነፃ

አትሌቲክስ ሻምፒዮና

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ግቢ፣ ኢምፔሪያል፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከቀጠናው እና ከዚያም ባሻገር የላቁ አትሌቶችን በማሰባሰብ ፍጥነት፣ ጥንካሬ እና ብርታት በሚተዋወቅበት ውድድር የሚያሳትፈውን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደሚያስተናግድ ሲያበስር በደስታ ነው። ልብ አንጠንጣይ ከሆኑ የአጭር ርቀት እና የረጅም ርቀት ውድድሮች ጀምሮ እስከ ዝላይ እና አሎሎ ውርወራ ድረስ የሚካሄድበት ይህ ዝግጅት ታላቅነትን ዒላማ አድርገው የሚሰሩት ተሳታፊዎች ያላቸውን አስደናቂ ተሰጥዖ እና ቁርጠኝነት ያሳያል። እጅግ ዘመናዊ መገልገያዎች እና ድጋፍ የተሞላበት ድባብ ያለው ውድድር አዳዲስ ክብረ ወሰኖችን ማስፈር ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ትውልድ አትሌቶች ተነሳሽነት እንደሚሰጥም እርግጥ ነው። የአትሌቲክስ ልህቀት መንፈስ እና የስፖርታዊ ጨዋነትን በምናከብርበት ሊታለፍ የማይገባ ዝግጅት ይቀላቀሉን!

amአማርኛ